በድሬዳዋ አስተዳደር የበልግ ወቅት የዝናብ ሁኔታ ሊያስከትል የሚችለውን አሉታዊ ተፅዕኖ ለመቀነስ የተሰጠ ቅድመ ማስጠንቀቂያ::
ድሬዳዋ 2 የዝናብ ወቅቶች፣ ማለትም ከመጋቢት አጋማሽ እስከ ግንቦት መጨረሻ የሚኖረው (የበልግ የዝናብ ወቅት) እና ከሀምሌ መጀመሪያ እስከ መስከረም አጋማሽ የሚኖረው (የክረምት የዝናብ ወቅት) እንዳሏት ይታወቃል:: በየወቅቶቹ በአስተዳደሩና በአጎራባች የኦሮሚያ ወረዳዎች በሚዘንበው ዝናብና በሚፈጠረው ደራሽ ጎርፍ ሳቢያ፣ በተለያዩ ጊዜያት በሰዎች ላይ የሞት፣ በንብረት ላይ ውድመት፣ እንዲሁም በእለት ተእለት የህብረተሰቡ የአኗኗር ሂደት ላይ ጉዳት ሲያስከትል ቆይቷል::…


