በዓለማቀፍ ደረጃ ለ43 ኛ እና በሀገራችን ለ26 ጊዜ ዛሬ ትምባሆ የማይጨስበት ቀን መከበር ጀመረ፡፡

    በዓለም ለ43ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ 26 ጊዜ ትምባሆ የማይጨስበት ቀን አስመልክተዉ በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብአት ቁጥጥር ዋና የሥራ ሂደት ወ/ሮ ሰሬዶ ኡመር ዛሬ ግንቦት 23(ሜይ 31 ) በዓለማቀፍ ደረጃ ትምባሆ የማይጨስበት የዓለም ቀን አስመልክተዉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጪያ ትምባሆ ማጨስን ማቆም ለሚፈልጉ ሰዎች ከመረጃ ጋር የተያያዘ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጅት በማጠናቀቅ ትምባሆ…

    Read More

      በምርጫ ወቅት ፓርቲዎች ሊያከብሯቸው የሚገቡ የሰብአዊ መብት አጀንዳዎች ይፋ ተደረጉ::

      የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን በስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሊያከብሯቸው የሚገቡ ባለ ስድስት ነጥብ የሰብአዊ መብቶች አጀንዳ ለተፎካካሪ ፓርቲዎች አቅርቧል። ፓርቲዎቹ እንዲያከብሯቸው የተቀመጡት የሰብአዊ መብቶች አጀንዳዎች፡- ተጨባጭ የሰብአዊ መብቶች እርምጃዎች ቃል ኪዳን፣ ለሰብአዊ መብቶች በቁርጠኝነት መቆም፣ ምርጫው ለስርዓተ ፆታ ምላሽ ሰጪ መሆኑን ማረጋገጥ፣ የሕግና ፖሊሲዎች ማሻሻያ ቃል ኪዳንን፣ የመንቀሳቀስ፣ የመደራጀት መረጃ የማግኘትና ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ…

      Read More

        በድሬደዋ ከተማ ለሚገኙ የከተማ ቀበሌዎች አመራሮች እና ባለሞያዎች በከተሞች ምግብ ዋስትና ሰትራተጂ ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን የድሬደዋ ከተማ የስራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ማርኮስ ባዩህ አስታወቁ፡፡

        በተጨማሪም በግንዛቤ ማስጨበጫው ላይ በሴፍቲኔት ፕሮግራም የሁለተኛው ዙር ምዕራፍ የተጠቃሚዎች አመላመል ላይ ለአመራሮችና ባለሞያዎች መግለጫ መሰጠቱን ለማወቅ ተችሏል፡፡ ምንጭ:የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ

        Read More

          በሐረሪ ብሄረሰብ ዘንድ በድምቀት የሚከበረውን የሸዋል ኢድ በዓል በዩኔስኮ የማይዳሰስ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝ ተገለፀ፡፡

          1442ኛው የሸዋል ኢድ በዓል በድሬደዋ የሐረሪ ብሄረሰብ ተወላጆች በዛሬው እለት በድሬደዋ ሚሊኒየም ፓርክ በድምቀት ተከብሯል፡፡ ከታላቁ የረመዳን ፆም ፍቺ አምስት ቀናት በኋላ ተከብሮ የሚውለው ሸዋል ኢድ በሐረሪ ብሄረሰብ ዘንድ በድምቀት እንደሚከበር የገለጹት በድሬደዋ የሃረሪ ኮሚዩኒቲ አስተባባሪ አቶ ዜዳን በክሪ በዓሉ በብሄረሰቡ ዘንድ ትልቅ ቦታ የሚሰጠው ነው ብለዋል፡፡በዓሉን በዩኔስኮ የማይዳሰሱ ቅርስነት ለማስመዝገብ ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ነው…

          Read More

            በሀገር ጉዳይ ላይ አንድ አይነት አቋም በመያዝ በጋራ መሰለፍ እንደሚገባ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የሆኑት አቶ ከድር ጁሀር አስታወቁ ።

            የሰላም ሚኒስቴር ከድሬዳዋ አስተዳደር ፍትህና ፀጥታ ጉዳዮች ቢሮ ጋር በጋራ በመሆን በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ 9 የከተማ እንዲሁም በ 38 ገጠር ቀበሌዎች ላይ በሚገኙ አካባቢዎች የሰላም ሚኒስቴር ባለሞያ በመመደብ ያለፍትን አራት ወራት ህብረተሰብ ተኮር የሆኑ ውይይቶች እንዲሁም የግለሰብ ችግር ፣ የአካባቢ ችግር ፣ የማህበረሰብ ችግር ፣ የአስተዳደር ችግርና የፌደራል ችግር በማለት ባሉት አጠቃላይ የፀጥታ ጉዳዮች ዙሪያ…

            Read More

              የውጪ ሀገራት በሀገራችን የውስጥ ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በድሬዳዋ አስተዳደር የሚኖሩ ወጣቶች አወገዙ ።

              ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሀገራችን ኢትዮጲያ እያከናወነችው ባለችው የልማትና የህግ-ማስከበር ስራዎች ብሎም የውስጥ ጉዳዮች ላይ የተለያዩ የውጪ ሀገራት ጣልቃ መግባታቸውን አስመልክቶ ” ድምፃችን ለነፃነታችን ” በሚል መሪ ቃል በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ወጣቶች አውግዘዋል ። ኢትዮጲያዊያን በሀገር ጉዳይ የማንደራደር ሀገር ወዳድ ህዝቦች እንደመሆናችን መጠን ለነፃነታችን የውጪ ጣልቃ ገብነትን በመቃወምና በአንድነት በመሆን በሀገራችን ላይ የተቃጣውን እኩይ ሴራ ማክሸፍ…

              Read More

                የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ የሴቶች ፖለቲካዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማሳደግ አበክሮ እንደሚሰራ ተገለፀ፡፡

                6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫን ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፅህፈት ቤት በድሬዳዋ አስተዳደር የምርጫ ቅስቀሳ ንቅናቄ አካሄደ ፡፡ በሀገራችን የሚካሄደውን 6 ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፅህፈት ቤት በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ 9 ኙም ቀበሌዎች ላይ እንዲሁም በገጠር ክላስተር የሚኖሩ ሴቶችን አሳታፊ ያደረገ የምርጫ ቅስቀሳ ንቅናቄ የተካሄደ ሲሆን በዚሁም…

                Read More

                  የድሬዳዋ አስተዳደር “አረንጓዴ ዐሻራ” አብይ ኮሜቴ በ2013ዓም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ውይይት አደረገ።

                  በድሬዳዋ አስተዳደር በ2013ዓም “አረንጓዴ ዐሻራ” የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን በተመለከት የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል እና የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ፅ /ቤት ሃላፊ አቶ ኤልያስ አልይ በአስተዳደር ደረጃ ሊተገበር የታቀደውን ተግባራት ዝርዝር እቅድ አቅርበዋል። በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርህ ግብር 2000000 ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ከነዚህም መካከል 200,000-500,000 ችግኞችን በጎረቤት ሀገራችን ጂቡቲ…

                  Read More

                    ሁሉን አካታች በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ሀገራዊ ውይይት በስነ-ፆታ ዕኩልነትና የሴቶች ተሳትፎ በኢትዮጲያ ፖለቲካ በሚል ሪዕስ በድሬዳዋ ራስ ሆቴል እየተካሄደ ነው።

                    በውይይቱ ከሶስት አጎራባች ክልሎች ማለትም ኦሮሚያ፣ ሐረሪ፣ ሶማሌ ክልልና ከድሬዳዋ አስተዳር የተውጣጡ ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት እየተሳተፉ ነው።

                    Read More

                      በየትምህርት ቤቱ የንባብ ማእከላትን ለማደራጀት በሚያስችል መልኩ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ ።

                      የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብት መጽሐፍት ኤጀንሲ፣ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲና ድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የንባብ ሣምንት በድሬዳዋ አስተዳደር በይፋ ተጀመረ ፡፡ ተማሪዎችና ወጣቶችን ማእከል በማድረግ ቀደምት የነበረውን የንባብ ባህልን በማጎልበትና በማሳደግ የተሟላና ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው ጠያቂና ምክንያታዊ የሆነ ትውልድ መፍጠር እንዲሁም አዳዲስ ሀሳቦችን መፍጠር የሚችልና በምክንያት የሚያምን ትውልድን ለመፍጠር ታልሞ “መጽሀፍት ለእውቀት ገበታ መዛግብት ለዘመን ትውስታ”…

                      Read More