በዓለማቀፍ ደረጃ ለ43 ኛ እና በሀገራችን ለ26 ጊዜ ዛሬ ትምባሆ የማይጨስበት ቀን መከበር ጀመረ፡፡

    በዓለም ለ43ኛ ጊዜ በሀገራችን ለ 26 ጊዜ ትምባሆ የማይጨስበት ቀን አስመልክተዉ በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የጤናና ጤና ነክ አገልግሎት ግብአት ቁጥጥር ዋና የሥራ ሂደት ወ/ሮ ሰሬዶ ኡመር ዛሬ ግንቦት 23(ሜይ 31 ) በዓለማቀፍ ደረጃ ትምባሆ የማይጨስበት የዓለም ቀን አስመልክተዉ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጪያ ትምባሆ ማጨስን ማቆም ለሚፈልጉ ሰዎች ከመረጃ ጋር የተያያዘ ድጋፎችን ለማድረግ ዝግጅት በማጠናቀቅ ትምባሆ ማጨስ ማቆምን በማበረታታት በማክበር ላይ መሆናቸውን ገለፁ፡፡
    የድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር በመሆን ትምባሆ ማጨስ ማቆምን በማበረታታት እንዲሁም በዓለማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየበዙ በሚገኙ ወረርሽኞች ምክኒያት በሰዎች ላይ እየደረሰ ያለዉን ጉዳት ለመቀነስ ዘርፈ ብዙ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን ገልፀዉ ከነዚህ ስራዎች አንዱ ትምባሆ ማጨስ ለሚፈልጉ ሰዎች ከመረጃ ጋር የተገናኙ ድጋፎችን ከማድረግ በተጨማሪ ትምባሆ ማጨስ በጤና ላይ የሚያስከትለዉን ጉዳቶች ላይ ግንዛቤ የማደበር እና በህግ እንዳይጨስበት የተከለከሉ ቦታዎች ላይ እንዳይጨስ የማሳወቅ እና የማስተባበር ስራ እየተሰራ መሆኑን አብራርተዋል፡፡