የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ ፍጥነት ያለውን የ 4 ጂ አገልግሎትን በድሬዳዋ አስተዳደር በይፋ አስጀመረ ።
ኢትዮ ቴሌኮም በምስራቅ ኢትዮጵያ ባሉ ከተሞች የሞባይል ኢንተርኔትን በላቀ ፍጥነት መጠቀም የሚያስችለውን የአራተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎትን በድሬዳዋ ያስጀመረ ሲሆን ፕሮግራሙም በድሬዳዋ፣ አይሻ እንዲሁም በጭሮ ከተሞች ላይ ተግባራዊ ይሆናል ። የኢትዮ ቴሌኮም እጅግ ዘመናዊ ብሎም ከፍተኛ ፍጥነት ያለውን የ 4 ጂ አገልግሎትን በድሬዳዋ አስተዳደር በይፋ ባስጀመረበት ወቅት በእለቱ የተገኙት የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ-አስፈፃሚ የሆኑት ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ…


