በጎረቤት አገራትና ታላላቅ ሃይቆች ክልል የሚገኙ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሚሲዮኖች ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዋና መስሪያ ቤት ጋር በመተባበር “የናይል ፍትሃዊ አጠቃቀም፣ የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ለክልላዊ ትብብር ያለው ሚና” በሚል ርእስ በተዘጋጀው የበይነ መረብ ውይይት ላይ ተሳትፈዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሊት በሶስቱ አገራት የሳይንቲስቶች ብሄራዊ ቡድን በወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት እንደሚካሄድ አቶ ደመቀ መኮንን ገልፀዋል።
የሶስትዮሽ ድርድሩ ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሄ መርህ መሰረት ውጤታማ እንዲሆን የአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ያላቸውን እምነት አረጋግጡ።
ግብፅና ሱዳን ጉዳዩን ዓለም አቀፋዊ በማድረግ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንዲደረግ ጥረት እያደረጉ ስለ መሆኑ አውስተዋል።
በስብሰባው ተሳታፊ የነበሩት የደቡብ ሱዳን ምክትል የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ጉዳዮች ሚኒስትር ደንግ ዳው ደንግ በበኩላቸው ታላቂ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ የሰላም ፕሮጀክት መሆኑን ገልፀዋል ፤ የሀገራቸው ፓርላማ በቅርቡ የናይል ስምምነት ማዕቀፍን እንደሚያፀድቅ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሶሰትዮሽ ድርድር ሁሉን ተጠቃሚ የሚያደርግ ስምምነት ላይ በመድረስ እልባት እንደሚያገኝ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።
በወቅቱም የታላቁ የኢትዮጵያ የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር የቴክኒክ ኮሚቴ ሰብሳቢ ኢንጂነር ጌዲዮን አስፋውና ሌሌች የዘርፉ ባለሙያዎች የውይይት መነሻ ፅሑፍ ማቅረባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
(ኤፍ.ቢ.ሲ)


