በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ በተሰሩ መጠነ ሰፊ ሥራዎች ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ ለሆኑ ቀበሌዎች የዕውቅና ሽልማት ተሰጠ፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ የሃይጅንና አካባቢ ጤና አጠባበቅ ክፍል በአስተዳደሩ ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የሆኑ የገጠር ቀበሌዎችን ሽፋን ለማሳደግ እያከናወነ ባለው ዘርፈ ብዙ ትግበራ የሁላ ሁሉል እና የኮርቱ ገጠር ቀበሌዎች ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ መሆናቸው ታውጇል፡፡
በሁለቱም ገጠር ቀበሌዎች በተከታታይ ሁለት ቀናት የዕውቅና አሰጣጥ መረሃ-ግብር የተከናወነ ሲሆን በመረሃ-ግብሮቹ ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ፣ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሙሉካ መሀመድ፣የአስተዳደሩ የጤና ቢሮ ሀላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶችና ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ለሁለቱ ገጠር ቀበሌዎች በእያንዳንዱ አባወራና እማወራ ደረጃ መፀዳጃ ቤት በመገንባት 100 ፐርሰንት ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ መውጣታቸው በመረጋገጡ የሜዳሊያ ፣ የዋንጫና ሰርተፊኬት ሽልማት ተሰጠ፡፡


