ምርጫው ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ::

    ግንቦት 28 ቀን ሊካሄድ የነበረው ሀገራዊ ምርጫ ሰኔ 14 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚካሄድ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
    ምርጫው የሚካሄደው የመራጮች ምዝገባ በተጠናቀቀባቸው ሁሉም ቦታዎች ብቻ ነው ተብሏል።
    ከመራጮች ምዝገባ ጋር ተያይዞ አቤቱታ የተነሳባቸው እና ምዝገባውን ዘግይተው የጀመሩ እና ያላጠናቀቁ የምርጫ ክልሎች እና ጣቢያዎች ላይ ግን ምርጫው በተጠቀሰው ቀን እንደማይካሄድ መገለፁን ኤፍቢሲ ዘግቧል።