የድሬደዋ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች ምዕራባዊያን በኢትዮጲያ የዉስጥ ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት ሊያቆሙ ይገባል ፣ የዉጭ ሀገራት ከኢትዮጲያ ላይ እጃቸዉን ያንሱ በሚል መሪ ቃል በኢትዮጲያ የወስጥ ጉዳዮች ላይ የሚያደርጉ ጣልቃ ገብነት አወገዙ፡፡
የድሬደዋ አስተዳደር የመንግስት ሰራተኞች ምዕራባዊያን በኢትዮጲያ የወስጥ ጉዳዮች የሚያደርጉትን ጣልቃ ገብነት በማዉገዝ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን በዚህ ስነስርዓት ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ባስተላለፉት መልዕክት እንደገለፁት
ለሀገራችን የበኩላችን ሚና መወጣት እንደሚገባ ምዕራባዊያን በኢትዮጲያ የወስጥ ጉዳዮች ላይ እያደረጉ የሚገኙትን ጣልቃ ገብነት በመቃወም ብሎም ለመከላከል እንደ ቀድሞ አባቶቻችን ሀገራችን ኢትዮጲያን ከማንኛዉም የዉጭ ወራሪዎችና ጣልቃ ገቦች ለመከለከል በአንድነት ልንቆም ይገባል ብለዋል ፡፡
በስነስርዓቱ ላይ የአስተዳደሩ ከንቲባና ምክትል ከንቲባን ጨምሮ የመስተዳደሩ የካቢኔ አባላትና ከፍተኛ አመራሮች ተሳትፈዋል፡፡


