የድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ከመማር ማስተማሩ እንዲሁም ከምርምር ስራዎች ጎን ለጎን በተለያዩ ሰብአዊ ድጋፎች ላይም በንቃት እየተሳተፈ ይገኛል ። ይህንንም ተከትሎ የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዘርፍ ለዳዊትና አሰገደች አረጋውያን መርጃ ድርጅትና ለድሬዳዋ የስጋ ደዌ ተጠቂዎችና አካል ጉዳተኞች ማህበር የምግብ ነክ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል ።
በ 2013 በጀት አመት ከኮቪድ ጋር ተያይዞ የተገዙ የምግብ ፍጆታዎችን ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸውና በድሬዳዋ አስተዳደር በተለያዩ የበጎ-አድራጎት ስራዎች ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች የምግብ ነክ ቁሳቁሶችን ድጋፍ በማድረግ ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም የሚያደርገውን መሰል የሰብአዊ ድጋፎችን ማድረጉን በስነ-ስርአቱ ላይ የተገኙት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶክተር ሰለሞን ዘሪሁን ተናግረዋል ።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም የተለያዩ ድጋፎችን በበጎ አድራጎት ስራዎች ላይ ለተሰማሩ ድርጅቶች ማድረጉን በእለቱ ድጋፍ የተደረገላቸው በበጎ-አድራጎት ስራዎች ላይ የተሰማሩ የድርጅት ሀላፊዎችና ተወካዮች ተናግረው በቀጣይም መሰል ድጋፎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ተናግረዋል ።


