የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዙ ድጋፎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተገፅዋል፡፡
ድጋፉን ያስረከቡት የፅ/ቤቱ ሃላፊ አቶ አብዱጁሃድ መሃመድ የበርካታ ዜጎችን ህይወት እየቀጠፈ ያለው የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ የበለጠ ጉዳት ሳያደርስ ለመከላከል የሚቻለው በሁሉም አካል እርብርብ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ከዚህ በመነሳት ፅ/ፈትቤታቸው ተከታታይ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
አክለውም ፅ/ቤቱ እንደ መሪ መስሪያቤት ለማህበረሰቡ ማህበራዊ አገልግሎትን ከመስጠት አንጻር የተጣለበትን ሃላፊነት ለመወጣት ሶስት መቶ ሺ ብር ወጪ በማድረግ 43 የኦክስጂን ሲሊንደሮችን ማበርከቱን ገልጸዋል፡፡ቀደምሲልም በተመሳሳይ መልኩ በሁለት መቶ ሺ ብር ወጪ የኦክሲጅን ሲሊንደሮችን ግዢ በመፈጸም በድጋፍ ማበርከቱን አብራርተዋል፡፡በቀጣይም ተመሳሳይ ድጋፎችን ለማበርከት እቅድ እንዳለ ጠቁመዋል፡፡
የድሬደዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ ለምለም በዛብህ የከተማ ስራ አስኪኃጅ ፅ/ቤት ላበረከተው ድጋፍ አመስግነው የኮሮና ቫይረስ ወረሽኝን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት የሚያግዙ ድጋፎች ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት እንዲሁም ከግለሰቦች እየተበረከተ መሆኑን ተናግረዋል፡፡


