በየትምህርት ቤቱ የንባብ ማእከላትን ለማደራጀት በሚያስችል መልኩ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ ።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ-መዛግብት መጽሐፍት ኤጀንሲ፣ ከድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲና ድሬዳዋ ባህልና ቱሪዝም ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የንባብ ሣምንት በድሬዳዋ አስተዳደር በይፋ ተጀመረ ፡፡ ተማሪዎችና ወጣቶችን ማእከል በማድረግ ቀደምት የነበረውን የንባብ ባህልን በማጎልበትና በማሳደግ የተሟላና ጥሩ ስነ-ምግባር ያለው ጠያቂና ምክንያታዊ የሆነ ትውልድ መፍጠር እንዲሁም አዳዲስ ሀሳቦችን መፍጠር የሚችልና በምክንያት የሚያምን ትውልድን ለመፍጠር ታልሞ “መጽሀፍት ለእውቀት ገበታ መዛግብት ለዘመን ትውስታ”…


