የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ ፍጥነት ያለውን የ 4 ጂ አገልግሎትን በድሬዳዋ አስተዳደር በይፋ አስጀመረ ።

    ኢትዮ ቴሌኮም በምስራቅ ኢትዮጵያ ባሉ ከተሞች የሞባይል ኢንተርኔትን በላቀ ፍጥነት መጠቀም የሚያስችለውን የአራተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎትን በድሬዳዋ ያስጀመረ ሲሆን ፕሮግራሙም በድሬዳዋ፣ አይሻ እንዲሁም በጭሮ ከተሞች ላይ ተግባራዊ ይሆናል ።
    የኢትዮ ቴሌኮም እጅግ ዘመናዊ ብሎም ከፍተኛ ፍጥነት ያለውን የ 4 ጂ አገልግሎትን በድሬዳዋ አስተዳደር በይፋ ባስጀመረበት ወቅት በእለቱ የተገኙት የኢትዮ-ቴሌኮም ዋና ስራ-አስፈፃሚ የሆኑት ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ እንዳሉት በተለይም በምስራቅ የሀገራችን አካባቢ ለሚገኙ ከ 330 ሺህ በላይ ደንበኞችን ተጠቃሚ የሚያደርገውን የአራተኛው ትውልድ የኢንተርኔት አገልግሎት ይፋ ማድረግ መቻሉን ገልፀው ይህም የላቀ የሞባይል ኢንተርኔት ፍጥነት መጠቀም የሚያስችል መሆኑንም ተናግረዋል።
    ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ አክለውም የ4ጂ የኢንተርኔት መሠረተ ልማት አገልግሎት በምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል ተዳራሽተሆን እንደተቻለና በተለይም በአዲስ አበባ እና ሌሎች ጥቂት የሀገሪቱ ከተሞች ብቻ ተወስኖ የነበረው ይሄው አገልግሎት ወደ 103 የክልል ከተሞች ለማዳረስ እየተሰራ መሆኑንም ዋና ስራ አስፈፃሚዋ በእለቱ ገልጸዋል ።
    ኢትዮ ቴሌኮም በምስራቅ ሪጅን ከአንድ ነጥብ ሦስት ሚሊየን በላይ ደንበኞች እንዳሉትና በሃገር አቀፍ ደረጃ ከ52 ሚሊየን በላይ የሞባይል ተጠቃሚዎች እንዳሉት በፕሮግራሙ ላይ ተገልፃል ።
    የኢትዮ ቴሌኮም ከፍተኛ ፍጥነት ያለውን የ 4 ጂ አገልግሎትን በድሬዳዋ አስተዳደር በይፋ ባስጀመረበት ስነ-ስርዓት ላይም የድሬደዋ አስተዳደር ምከትል ከንቲባ አህመድ መሐመድ ቡህንና ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የአስተዳደሩ አመራሮች ፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ሀላፊዎችና ሰራተኞች የአስተዳደሩ ነዎሪዎች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን በዝግጅቱ ላይም በእጣ የሚወጡ የሞባይል ስልኮችና ራውተሮችን በማዘጋጀት ለበርካታ ባለ እድለኛ ደንበኞችም አበርክቷል ።