የድሬዳዋ አስተዳደር “አረንጓዴ ዐሻራ” አብይ ኮሜቴ በ2013ዓም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ውይይት አደረገ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር በ2013ዓም “አረንጓዴ ዐሻራ” የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርን በተመለከት የግብርና ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ምክትል እና የግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ፅ /ቤት ሃላፊ አቶ ኤልያስ አልይ በአስተዳደር ደረጃ ሊተገበር የታቀደውን ተግባራት ዝርዝር እቅድ አቅርበዋል።
    በዘንድሮ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርህ ግብር 2000000 ችግኞችን ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው ከነዚህም መካከል 200,000-500,000 ችግኞችን በጎረቤት ሀገራችን ጂቡቲ ለመትከል በቅድሚያ ተይዞ እየተሰረ መሆኑን ገልፀዋል ።
    የድሬዳዋ አስተዳደር “አረንጓዴ ዐሻራ” አብይ ኮሜቴ ሳብሳቢ አቶ ኢብራሂም ዩሱፍ እንደገለጹት ዘንድሮም ካለፉት አመታት ከገኘነው ልምድ በመነሳት በአገር አቀፍ ደረጃ ሰባት ቢሊዮን ችግኞች ለመትከል ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን ገልፀው እንደ አስተዳደር በቀረበው እቅድ ላይ ሊነሱ የሚችሉ ነገሮች ካሉ እንዲነሱ ለኮሚቴ አባላት እድል ሰጥተዋል።
    የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር የዘንድሮውን “ኢትዮጵያን እናልብሳት” በሚል መሪ ሃሳብ በሚተገበረው የ2013 አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር በመርሃ ግብሩ 7 ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የታቀደ 2(ሁለት) ሚሊዬን ችግኞችን እንደ አስተዳደር ለመትከል መታቀዱን ገልፀውለእቅዱ ስኬት ሁሉምየአስተዳደራችን ነዋሪዎች ተሳትፎ ወሳኝ መሆኑ ተመልክቷል።
    በመጨረሻም አረንጓዴ ዐሻራ አብይ ኮሜቴ አባላት በአስተዳደር ሊተገበር በታቀደው የአረንጓዴ አሻራ መርህ ግብር ስኬት እየተከናወኑ ያሉ ተግባራትን በተመለከተ የመስክ ምልከታ አድርገዋል ።
    ምንጭ፦ድሬዳዋ ግብርና ቢሮ