6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫን ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፅህፈት ቤት በድሬዳዋ አስተዳደር የምርጫ ቅስቀሳ ንቅናቄ አካሄደ ፡፡
በሀገራችን የሚካሄደውን 6 ተኛውን ሀገራዊ ምርጫ ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፅህፈት ቤት በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ 9 ኙም ቀበሌዎች ላይ እንዲሁም በገጠር ክላስተር የሚኖሩ ሴቶችን አሳታፊ ያደረገ የምርጫ ቅስቀሳ ንቅናቄ የተካሄደ ሲሆን በዚሁም ፕሮግራሙ ላይም ተሳታፊ የሆኑ ሴቶች ብልፅግና ፓርቲ እንደ ሀገር እየሰራቸው ያሉትን ኢኮኖሚያዊ ፣ ፖለቲካዊና ማህበራዊ ስራዎች የሚያወድሱ የተለያዩ መፈክሮችን በፕሮግራሙ ላይ በመያዝ ታድመዋል ፡፡
በ 6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በድሬዳዋ አስተዳደር 9 የፖለቲካ ፓርቲዎች እየተወዳደሩ ሲሆን የብልፅግና ፓርቲም ከነዚህ ተወዳዳሪ ፓርቲዎች ውስጥ አንዱ መሆኑን የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት አ/ቶ መብራቴ ገብረየስ ተናግረው የሴቶች ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ተሳትፎና ተጠቃሚነትን ለማሳደግም ፓርቲው አበክሮ እንደሚሰራ አቶ መብራቴ በእለቱ ተናግረዋል ፡፡
ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች የሀገር ምሶሶ መሆናቸውን በማመን በድሬዳዋ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር ላይ ሴቶችን ከማሳተፍ ባለፈ ለ 6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫም ለምክር ቤት በእጩነት 44 ፐርሰንት የሚሆኑ ሴት ተወዳዳሪዎች የቀረቡ ሲሆን በትምህርት ዝግጅታቸውም የላቁ መሆናቸውን የድሬዳዋ ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ወ/ሮ ፈጡም ሙስጠፋ ተናግረዋል፡፡
በድሬዳዋ አስተዳደር የሚገኙ ሴቶችን አሳታፊ ያደረገ የምርጫ ቅስቀሳ ፕሮግራም በማካሄድ በቀጣይ በሚካሄደው 6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫ ላይ ከብልፅግና ፓርቲ ጎን ሊሆኑ እንደሚገባም የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ሴቶች ሊግ ፅህፈት ቤት ሀላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሁክሚያ መሀመድ ተናግረዋል


