ማህበረሰቡ በአመጋገብ ሰርአቱ ምግብን አመጣጥኖ ቢመገብ በሀገራችን ያለውን የስርአተ ምግብ ችግሮችን ለመቅረፍ ከፍተኛ ሚና እንዳለው ተገለፀ።
የአስተዳደሩ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለ9 የመንግስት ተቋማት የስርአተ ምግብ ተወካዮች እና ለባለድርሻ አካላት በ1000 ቀናት(ከፀንስ እስከ ሁለት አመት ዕድሜድረስ)፣በስርአተ ምግብ ፖሊሲ ዙሪያ ግንዛቢና በቀጣይ ችግሩን ለመቅረፍ የአሰራር አግባቡ ላይ የምክክር መድረክ አካሄዷል። በሀገራችን የስርአተ ምግብ ችግር በዜጎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ምግብን አመጣጥኖ መመገብ ቅንጦት አለመሆኑን በመገንዘብ በአመጋገብ ስርአታችንን በአካባቢያችን የሚገኙ…


