የአስተዳደሩ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ለ9 የመንግስት ተቋማት የስርአተ ምግብ ተወካዮች እና ለባለድርሻ አካላት በ1000 ቀናት(ከፀንስ እስከ ሁለት አመት ዕድሜድረስ)፣በስርአተ ምግብ ፖሊሲ ዙሪያ ግንዛቢና በቀጣይ ችግሩን ለመቅረፍ የአሰራር አግባቡ ላይ የምክክር መድረክ አካሄዷል።
በሀገራችን የስርአተ ምግብ ችግር በዜጎች ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ከፍተኛ በመሆኑ ምግብን አመጣጥኖ መመገብ ቅንጦት አለመሆኑን በመገንዘብ በአመጋገብ ስርአታችንን በአካባቢያችን የሚገኙ ተፈጥራዊ ምግቦችን በመመገብ ሊያስከትለው የሚያስችለው ችግሮች ለመቅረፍ ያስችለናል ያሉት የአስተዳደሩ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀርቢ ቡህ ሲሆኑ ማህበረሰቡ ይህን ችግር ከግምት ውስጥ በማስገባት የራሱን ሆነ የቤተሰቡን ጤና ሊጠብቅ ይገባል ብለዋል ።


