በደም እጥረት ሳቢያ ክቡር የሆነው የሰው ልጆ ህይወት እንዳያልፍ ሁሉም ሰው ደም በመለገስ የድርሻውን ሊወጣ ይገባል ተባለ ፡፡

    የድሬዳዋ አሰተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን አመራሮች እና አባሎች በዛሬው እለት የደም መለገስ ፕሮግራም አካሂደዋል ፡፡
    የድሬደዋ አስተዳደር የደም ባንክ አገልግሎት ጽ/ቤት ሀላፊ የሆኑት አቶ ፋሲል ዘውዴ ለድሬደዋ ፖሊስ ሚድያ እንደገለፁት በደም እጥረት ሳቢያ ክቡር የሆነው የሰው ልጆ ህይወት እንዳያልፍ ሁሉም ሰው ደም በመለገስ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ተናግረው የድሬደዋ የደም ባንክ አገልግሎት በተለያየ ሁኔታ የደም እጦት የሚያጋጥማቸው ዜጎች ህይወታቸውን ለመታደግ በሚያደርገው የደም መሰብሰብ ሂደት በስራ ቦታም ሆነ ደም ባንክ ድረስ በመቅረብ ደም በመለገስ እረገድ በግምባር ቀደምትነት የድሬደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ተጠቃሽ ነው ለዚህም ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል::
    ሀላፊው አያይዘውም ይሄው ለሌሎችም ምሳሌ የሆነ የሰብአዊነት ተግባር በቀጣይም በተቋሙም ሆነ በአባልና አመራር ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታልም ብለዋል ፡፡
    ደም እየለገሱ ካገኘናቸው አባሎች መካከል ም/ሳጅን አካለ ወርቅ ዳመነ አንዱ ሲሆን ከእሱ ጋር ባደረገው ቆይታ እንደተናገው ከአሁን በፊት አደጋ ደርሶበት በከፍተኛ ሁኔታ ደም ፈሳት እንደነበረ እና ሰዎች በለግሱት ደም ህይወቱ መትረፉን ተናግሮ ዛሬ የምንለግሰው ደም ውድ የሰው ልጅ ሂወት ለመታደግ የሚውል እና ተመልሶ ለኔም ሊውል ይችላል ብዬ ስለተረዳሁ ነው ሁሉም ሰው ይህንን ተረድቶ ደም በመለገስ የሌሎችን ሂወት መታደግ ይኖርበታል ብሏል ፡፡
    ሌሎች ያነጋገርናቸው አመራሮች እና አባሎች ደም በመለገሳቸው ትልቅ ደስታ እንደተሰማቸው ገልፀው ሁሉም ሰው ደም በመለገስ የሰው ልጅ ህይወት ለመታደግ ሊረባረብ ይገባል ሲሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
    ድሬ ፖሊስ