በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል እሚደርሱ የትራፊክ አደጋዎችን በጋራ በመከላከልና በመቆጣጠር እንደሁም በትራንስፖርት ዘርፍ ላይ የሚስተዋሉ የአሰራር ክፍተቶችንና የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በጋራ ፈትሾ በመፍታት ለተገልጋዩ እርካታ እንደሚሰሩ በምስራቅ ኢትዮጵያ የሚገኙ የትራንስፖርት ጽ/ቤት አመራሮች አስታወቁ፡፡
ጽ/ቤቶቹ የ2013 በጀት አመት ጥምር የጋራ እቅድ አፈጻፀም መድረካቸውን አካሂደዋል፡፡ በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል ከአሽከርካሪዎችና እግረኞች እንደሁም የመልካአምደሩ ፈታኝነት ጋር ተያይዞ በየአመቱ በትራፊክ አደጋ ሳቢያ በርካቶች ለህልፈት ሲዳረጉ ጥቂት የማይባሉቱ ደግሞ ከከባድ አካል ጉዳት እስከ ንብረት ውድመት ለሚደርስ ችግር እየተጋለጡ ይገኛሉ፡፡ በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ የተመራው በድሬደዋ የትራንስፖርት ዘርፍ አመራሮች…


