ጽ/ቤቶቹ የ2013 በጀት አመት ጥምር የጋራ እቅድ አፈጻፀም መድረካቸውን አካሂደዋል፡፡
በምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል ከአሽከርካሪዎችና እግረኞች እንደሁም የመልካአምደሩ ፈታኝነት ጋር ተያይዞ በየአመቱ በትራፊክ አደጋ ሳቢያ በርካቶች ለህልፈት ሲዳረጉ ጥቂት የማይባሉቱ ደግሞ ከከባድ አካል ጉዳት እስከ ንብረት ውድመት ለሚደርስ ችግር እየተጋለጡ ይገኛሉ፡፡
በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ የተመራው በድሬደዋ የትራንስፖርት ዘርፍ አመራሮች በሀረርና ጅግጅጋ በመገኘት ከምስራቁ አጎራባች ክልሎች የትራንስርት ሴክተሩ አመራሮች እንደሁም የትራፊክና ፀጥታው ዘርፍ ተጠሪ አካላት ጋር ዘመናዊና ቀልጣፋ እንደሁም ከፀጥታ ስጋት ነፃ የሆነ የትራንስፖርት አገልግሎትን ተደራሽነት ላይ ውይይት አካሂደዋል፡፡
በዚህም የተቀናጀ አሰራርን በማስፈን ረገድ ፍተቶቻችን ነው ባሉዋቸው ጉዳዮች ላይ በመወያየት በቀጣይሊታረሙ እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በመድረኮቹ ላይ የሀረሪ ምስራቅ አሮሚያና ሱማሌ ክልሎች እንዲሁም የድሬደዋ አስተዳደር የ2013 በጀት አመት ጥምር የጋራ እቅድ አፈጻፀም ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡
በዚህም በተለይ የድሬደዋ አስተዳደር በሁሉም መልኩ ከክልል ባለፈ በሀገር አቀፍ ደረጃ ተጠቃሽ የሆኑ መልካም ስራዎችን መስራቱን ያነሱት የመድረኩ ተሳታፊዎች በተለይ የልዩ ባሶችን ወደመናኸሪያ ማስገባቱ፣የፍጥነነት መገደቢያ መሳሪያን በፍጥነት ለማስተግበር የሄደበት ፍጥነት እንደሁም ከትራፊክ ፖሊሶችና የፀጥታው አካል ጋር በእቅዶቹ ላይ እየሰራ ያለው ጥምርታዊ እንቅስቃሴና የሌሊት ባጃጆችን በተመለከተ የሰራው ስራ እንደተሞክሮ ወስደው እንደሚተገብሩት ክልሎቹ ተናግረዋል፡፡
በትራንስፖርት ባለስልጣን ድሬደዋ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰአዳ አዋሌ በበኩላቸው እንደ ድሬደዋ አስተዳደር ትራንስፖርት ባለስልጣን ቅርንጫፍ ጽ/ቤት በክልሎቹ ጉብኝት ማድረጋችንና ተሞክሮን ለመጋራትና ለማጋራት ያደረግነው እንቅስቃሴ ባንድ ክልል ብቻ የተወሰነ ውጤት ለብቻው ውጤት ስለማያመጣ የትራንስርት ዘርፉን በእኩል በማዘመንና ብልሹ አሰራሮችን በጋራ በመታገል እንደሁም ህገወጥ እንቅስቃሴዎች ላይ የተጠናከረ እርምጃን በመውሰድ ነው ብለዋል፡፡
በቀጣይ የተሻለ ውጤትን እንደምስራቁ የሀገሪቱ ክፍል ለማስፈን የእለቱ ውይይት እገዛው የጎላ ስለመሆኑ ተናግረዋል፡፡
የእለቱ የድሬደዋ ልኡካን በሀረሪና ጅግጅጋ ክልሎች ላይ ያደረጉት ጉብኝትም ውጤታማ እንደነበር ወ/ሮ ሰአዳ ገልፀዋል፡፡
ምንጭ፦Federal Transport Authority Dire Dawa Branch


