በድሬዳዋ አስተዳደር ጤና ቢሮ አስተባባሪነት ከዘጠኝ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተውጣጡ የስርአተ ምግብ ተጠሪዎች በገጠር ቀበሌዎች ያለውን የስርአተ ምግብ ኮሚቴዎችን ለማጠናከርና በትምህርት ቤቶች ያለውን የምገባ ስነ ስርአት አስመልክቶ ድጋፍና ክትትል ተግባር አከናውነዋል።
የስርአተ ምግብ ተጠሪዎች በጀልዴሳ ክላስተርና በቢያአዋሌ ክላስተር ለሁለት ተከታታይ ቀናት ባደረገው ምልከታ በገጠሩ በስርአተ ምግብ ዙሪያ የተቋቋመው ኮሚቴ በሙሉ ቁመናው ወደ ተግባር ባለመግባቱ እየተከሰተ ያለውን የመቀንጨር ችግር እንዳይባባስ ኮሚቴው ጊዜ ሳይሰጥ ወደ ስራ መግባት እንዳለበትና ባለድርሻ ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍ በማድረግ በምግብ እጥረት ምክንያት እየተከሰተ ያለውን የመቀንጨር ችግር ላይ ርብርብ በማድረግ መስራት ይኖርብናል ብለዋል። ኮሚቴው በጀልዴሳና…


