የምርምር ጽሁፎች ማቅረቢያ መጽሔት በምሁራን መካከል ጠንካራ ትስስር እንዲኖር ትልቅ አስተዋፆኦ እንደሚኖረው ተገለፀ ።
የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሃርላ የተሰኘ የምርምር ጽሁፎች ማቅረቢያ መጽሔት (journal) አስመረቀ፡፡ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግት ምክትል ፕሬዝዳንት ፅህፈት ቤት የተዘጋጀውና ከድሬዳዋ ከተማ 12 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ጥንታዊዋ የሃራላ ከተማ ስም የተሰየመው የምርምር ጽሁፎች ማቅረቢያ መጽሔት (journal) በድሬዳዋ ዩኒቨርስቲ ተመርቋል ። በዚሁም የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ በመገኘት ንግግር ያደረጉት የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶክተር ኡባህ…


