ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ እንደሚገኝ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

    ሰኔ 14/2013 ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ እንደሚገኝ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ። የአስተዳደሩ የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ ለፋና እንደተናገሩት ምርጫው በሠላም ይጠናቀቅ ዘንድ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል። ይህም ለማድረግ ያስችል ዘንድ የተለያዩ የአስተዳደሩ የፀጥታ አካላት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ከቅድመ ምርጫ ዝግጅት ጀምሮ በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አስታውቀዋል። ምንጭ፡-ከዋልታ

    Read More

      የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ድምጽ ሰጡ ሰኔ 14 ፣ 2013 የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሐመድ ቡህ በስድስተኛው ሃገራዊ ምርጫ ድምፃቸውን ሰጡ።

      በድሬዳዋ አስተዳደር በከዚራ መንደር ሁለት የምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምፃቸውን የሰጡት አቶ አህመድ በድሬዳዋ ዛሬ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫው በሠላም እየተካሄደ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ምክትል ከንቲባው ድምፃቸውን ከሰጡ በኋላ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል። ምንጭ፡-FBC

      Read More