ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ እንደሚገኝ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ

    ሰኔ 14/2013 ምርጫው በሰላማዊ መንገድ እየተካሄደ እንደሚገኝ የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።
    የአስተዳደሩ የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መግራ ለፋና እንደተናገሩት ምርጫው በሠላም ይጠናቀቅ ዘንድ ዘርፈ ብዙ ስራዎች መሠራታቸውን ገልጸዋል።
    ይህም ለማድረግ ያስችል ዘንድ የተለያዩ የአስተዳደሩ የፀጥታ አካላት ከህብረተሰቡ ጋር በመሆን ከቅድመ ምርጫ ዝግጅት ጀምሮ በቅንጅት ሲሰራ መቆየቱን አስታውቀዋል።
    ምንጭ፡-ከዋልታ