በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር ድምፅ እንዳይሰጥባቸው በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ተከልክለው የነበሩ 6 የምርጫ ጣቢያዎች በዛሬው እለት ድምፅ እንዲሰጥባቸው የብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ወስኗል።
እነዚህ 6 የምርጫ ጣቢያዎች የመራጮች የምዝገባ ሂደት ከምርጫ ቦርድ እውቅና ውጭ አካሂደዋል ተብሎ ነበር ምርጫ እንዳይካሄድባቸው ውሳኔ የተሰጠው። የምርጫ ተወዳዳሪ ፓርቲዎችና ህብረተሰቡ ባቀረቡት ቅሬታና ጥያቄ መሰረት መራጮች የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብት ስላላቸው ምርጫ ቦርድ በእነዚህ 6 የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ እንዲካሄድ ውሳኔ አስተላልፏል። መራጮች ከዚህ በፊት የተመዘገቡበትን የምርጫ ካርድ ይዘው መጥተው እንደ አዲስ እየተመዘገቡ መምረጥ እንደሚችሉ ምርጫ ቦርድ ገልጿል፡፡
በተመስገን ሽፈራው
ምንጭ፡-EBC


