ኮምሽኑ በዛሬው እለት 6ተኛው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ በሰላም መጠናቀቁን አስመልክቶ ለተለያዩ የሚዲያ አካላት መግለጫ ሰተዋል፡፡
የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር አለሙ መግራ በመግለጫቸው እንደተናገሩት የድሬዳዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ከምርጫ በፊት አቅዶ ወደ ስራ መግባቱን አስተውሰው በዚሁ መሰረት ምርጫው በተካሄደባቸው ሁሉም የከተማ እና ገጠሩ ቀበሌዎች ምርጫው ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም ተካሄዶ መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
ከተለያዩ የጸጥታ አካላት ጋር በመሆን የምርጫ ኮሮጆ የመጠበቅ እና የማጀብ እንዲሁም ለታዛቢዎች እና ለሚዲያ አካላት ጥበቃ የማድረግ ስራዎች በዋነኝነት መከናወናቸውን የተናገሩ ኮሚሽነር አለሙ መግራ
ለምርጫው ፍፁም ሰላማዊነት ቀን እና ለሊት ሲተጉ ለነበሩ የድሬዳዋ ፖሊስ አባላት እና ሌሎች የጸጥታ አካላት እንዲሁም ለመላው የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች የላቀ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡


