#ድሬዳዋ ስልጡን ሕዝብ – ስልጡን ከተማ
የድሬዳዋ ሕዝብ ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ይወክሉኛል ይመሩኛል ያላቸውን ተወካዮቹን ያለአንዳች ኮሽታ በመምረጥ ተደጋግሞ እንደሚባለውም ስልጡን ሕዝብ መሆኑን አስመስክሯል።
6ኛው አገራዊ ምርጫ በቅድመ ምርጫው ሂደትና በምርጫው እለት ያለምንም ችግር ሊከናወን የቻለው በሕዝባችን አገር ወዳድነትና አርቆ አስተዋይነት በመሆኑ በከተማም በገጠርም ለሚኖሩ ለመላው የአስተዳደራችን ነዋሪዎች ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
በተጨማሪም ይሔ ምርጫ ተጀምሮ እስኪፈፀም ድረስ የፀጥታ ችግር እንዳይኖርና ሰላማዊ ሆኖ እንዲከናወን ቀን ከሌት ለሰሩ ለአስተዳደሩ እና ለፌዴራል የፀጥታ አካላት ምስጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ ።
እንዲሁም የኢትዮጵያን የዲሞክራሲ ችግኝ ለመትከል በሚደረገው ጥረት ውስጥ መልካም አስተዋጽኦ ላበረከታችሁ ተፎካካሪ ፓርቲዎች ፣ የምርጫ ቦርድ አመራርና ሰራተኞች ፣ ሚዲያዎች፣ ታዛቢዎች፣ የምርጫ አስፈፃሚዎችና ሲቪክ ማኅበራት በሙሉ ምስጋናዬ ይድረሳችሁ።
መሐመድ አህመድ ቡህ
የድሬዳዋ አስተዳደር ም/ከንቲባ
ሰኔ 15/2013 ዓ.ም ድሬዳዋ


