የድሬዳዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሀመድ ቡህ የ6ኛውን አገር አቀፍ ምርጫ በስኬት መጠናቀቅ አስመልክተው መልእክት አስተላልፈዋል::
#ድሬዳዋ ስልጡን ሕዝብ – ስልጡን ከተማ የድሬዳዋ ሕዝብ ለሚቀጥሉት አምስት አመታት ይወክሉኛል ይመሩኛል ያላቸውን ተወካዮቹን ያለአንዳች ኮሽታ በመምረጥ ተደጋግሞ እንደሚባለውም ስልጡን ሕዝብ መሆኑን አስመስክሯል። 6ኛው አገራዊ ምርጫ በቅድመ ምርጫው ሂደትና በምርጫው እለት ያለምንም ችግር ሊከናወን የቻለው በሕዝባችን አገር ወዳድነትና አርቆ አስተዋይነት በመሆኑ በከተማም በገጠርም ለሚኖሩ ለመላው የአስተዳደራችን ነዋሪዎች ላቅ ያለ ምስጋናዬን አቀርባለሁ። በተጨማሪም ይሔ ምርጫ…


