የድሬዳዋአስተዳደርየሰላምምክርቤት ለ6ኛ ጊዜበ አገራችንና በከተማ አስተዳደራችን የተካሄደውን ምርጫ አስመልክቶ ሰኔ 17/10/2013 ዓ.ም ግምገማ አካሄደ፡፡
በግምገማ መድረኩ የአስተዳደሩ ም/ከንቲባ አቶ አህመድ ቡህ፣የአስተዳደሩ ም/ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ ከዲር ጆሀር፣የፍትህ ፀጥታና ህግ ጉዳዬች ቢሮ ሃላፊ አቶ ሙሳ ጠሐ፣የደሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አለሙ መገራን ጨምሮ ከፍተኛ የአስተዳደሩና የፌደራል የፀጥታና የፍትህ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች የተገኙ ሲሆን በተጨማሪም በከተማችን በምርጫው ተሳታፊ የነበሩ የፖለቲካ ፓርቲ ተወካዬች፣የሃይማኖት ተቋማት ተወካዬች፣የአገር ሽማግሌዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው ባለድርሻ…


