የህዝቡን ውሳኔ በፀጋ በመቀበል ለተግባራዊነቱም እንደሚተጉ በድሬዳዋ የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ:
የድሬዳዋ አስተዳደር የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የ2013 ዓ.ም 6ኛውን አገር አቀፍ ምርጫ አስመልክቶ በዛሬው እለት መግለጫ ሰጥቷል:: ምክር ቤቱ በመግለጫው በዘንድሮው ምርጫ ላይ የተለያዩ አካላት አሉታዊ ተፅእኖ ለማሳደር ጥረት ቢያደርጉም የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪ ተፅእኖውን ተቋቁሞ ሰላማዊ ምርጫ ማድረግ በመቻሉ የተሰማውን ደስታ ገልጿል:: በአስተዳደሩ በምርጫው የተሳተፉት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከቅድመ ምርጫ እንቅስቃሴ ጀምሮ እስከ ድምፅ መስጫው…


