በድሬዳዋ አስተዳደር በ 6 ተኛው ዙር ሀገራዊ ምርጫ ላይ የሚወዳደሩ 5 ተፎካካሪ ፓርቲዎች የተሳተፉበት የምርጫ ክርክር በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ ፡፡
በ 6 ተኛው ሀገራዊ ምርጫ በድሬዳዋ አስተዳደር 9 የፖለቲካ ፓርቲዎች ይወዳደራሉ፡፡ ሀገራዊ ምርጫውም ከመካሄዱ በፊት በምርጫው ላይ ለሚወዳደሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ መድረክ በማመቻቸት ፖሊሲያቸውን ለምሁራ ለነዋሪዎች ብሎም ለደጋፊዎቻቸው ሀሳባቸውን ያቀርቡ ዘንድ መድረክ አመቻችቷል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀው መድረክ ላይም ብልፅግና ፓርቲ ፣ እናት ፓርቲ ፣ ኢዜማ ፓርቲ ፣ አብን ፓርቲ እንዲሁም ኢ.ሶ.ዴ.ፓ ፓርቲ ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን…


