በሀገራችን ላይ በሚደረጉ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ መስኮች ላይ ከመንግስት ጋር በጋራ በመሆን እንደሚሰሩ የድሬዳዋ አስተዳደር ነዋሪዎች ተናገሩ ።
በዛሬው እለትም በሀገራችን ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ በድሬዳዋ አስተዳደር በሚገኙ የተለያዩ የከተማ ቀበሌዎች ውይይት ተካሂዷል። የድሬዳዋ አስተዳደር በርካታ ብሄር ብሄረሰቦች ፣ ሀይማኖቶች በጋራ ፣ በፍቅርና በአንድነት ተቻችለውና ተከባብረው የሚኖሩባት ከተማ ስትሆን የከተማዋ ነዋሪዎችም በተለያዩ ጊዜያቶች በሀገራችን ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በጋራ ከመንግስት ጋር በመወያየት ከመፍታት ባለፈ ድጋፍ በሚያስፈልጋቸው ጉዳዮች ዙሪያም ቢሆን በግንባር ቀደምትነት በመሰለፍ ድጋፍ ሲያደርጉ ቆይቷል…


