የድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች በሱማሌ ክልል ሲቲ ዞን ገርበኢሴ ከተማ የተፈፀመውን የጅምላ ግድያና ማፈናቀል በመቃወም በምድር ባቡር አደባባይ ሰልፍ አካሄዱ።
ኡጉጉማ በሚባለው የጥፋት ቡድን በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግድያና ማፈናቀል ያወገዙት የድሬደዋ ነዋሪዎች የንፁሀንን ደም ያፈሰሱ ወንጀለኞች ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል። በሰልፉ ላይ ከንቲባ አህመድ ቡህ ፣ ምክትል ከንቲባ ከድር ጁሀር እና የሱማሌ ክልል ንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ አቶ በሽርን ጨምሮ የአገር ሽማግሌዎች እና የወጣት ተወካዮች መልእክት አስተላልፈዋል። የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና በሺዎች የሚቆጠሩ የድሬዳዋ ነዋሪዎች በተሳተፉበት…


