ለሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ለክብሩና ለፍቅሩ የሚያደርጉትን ድጋፍ ይበልጥ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ነዋሪዋች ገለፁ።

    በድሬዳዋ አስተዳደር ቀበሌ 02 ኩባ ካፕ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በምገኘው የኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሆስፖታል ጉዳት ለደረሰባቸው ለኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት በአካባቢው የሚኖሩ የማህበረሰብ ክፍሉች በራሳቸው ተነሳሽነት ከ 43 ሺ ብር በላይ በሬና የፊጆታ እቃዎችን ድጋፍ አበርክተዋል።
    ቀደም ሲል በኢፌዲሪ ሰራዊት የአየር ሃይል አባል የነበሩ እና በጡረታ ከሰራዊቱ የተገለሉት በአሁን ወቅት በዶሮ ዕርባታ የተሰማሩት አቶ አለማየሁ ማስረሻ 180 ዶሮዎችን ድጋፍ አድርገዋል።
    በድጋፍ ርክክቡ ነዋሪዎችን ወክለው ንግግር ያደረጉት አቶ ዳንኤል ጌታቸው እንደገለፁት የሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ለሀገራችን ህልውና እያበርከተ ለሚገኝው ከፍተኛ አስተዋፆኦ በፍቅር ለሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ክብር የምናደርገው ድጋፍ ይበልጥ ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉም ገልፀዋል።
    የኢፌዲሪ የሀገር መከላከያ ሰራዊት ሆስፒታል ተወካይ ኮሎኔል ብርሃኑ ዘውዴ በንግግራቸው የድሬደዋ ህዝብ ለሀገር መከላከያ ሰራዊታችን እያደርገ ላለው ከፉተኛ ፍቅር እና ድጋፍ በማመስገን ሁላችንም ለአንዷ ሀገራች በሞያችን ከቆምን የሀገራችንን ክብር ከፍ ማድረግ እንችላለን ያሉ ሲሆን ለድጋፍ አድራጊዎችም የመስጋናና የምስክር ወርቀት አበርክተዋል።