ለመላው የእስልምና ሀይማኖት ተከታዮች መልካም የኢድ አልአድሃ ( አረፋ) በዓል!!

    የድሬዳዋ አስተዳደር መንግስት ኮሙዪኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች እንኳን ለ1442ኛው ዓመተ-ሒጅራ ለሚከበረው የኢድ አልአድሃ (አረፋ) በዓል በሰላምና በጤና አደረሳችሁ እያለ መልካም ምኞቱን ይገልፃል ::
    በዓሉ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት በተጠናቀቀበት ማግስት የሚከበር በመሆኑ በዓሉን ደማቅና ልዩ ያደርገዋል ::
    የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፉ አቶ እስቅያስ ታፈሰ የሁለተኛው ዙር የህዳሴው ግድብ በመጠናቀቁ መላው የኢትዮጵያ ህዝቦች እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል። መልካም የኢድ አልአድሃ (አረፋ) በዓል እንዲሆንላችሁ በድጋሚ መልካም ምኞታቸውን ተመኝተዋል::
    ቀን 12/11/2013 ዓ.ም