ለመላው የአስተዳደራችን እንዲሁም የሀገራችን የእስልምና ሃይማኖት
ተከታዮች በሙሉ ፤ በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት ለሚከበረው ለ1ሺ 442ኛው ዓመተ-ሂጅራ የኢድአል አድሃ – አረፋ በአል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ … አደረሰን ፤
ኢድ ሙባረክ !
በተጨማሪም መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ለውጪ ጠላትና ለአገር ውስጥ ባንዳ ሳይበገር ከገንዘብ ማዋጣት እስከ ዲፕሎማሲ በአንድነት ተሰልፎ ባደረገው ርብርብ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 2ኛ ዙር የውሀ ሙሌት በስኬት በመጠናቀቁ እንኳን ደስአላችሁ ለማለት እፈልጋለሁ።
የኢትዮጵያ ሰላምና ልማት የማይዋጥላቸው የውጪና የውስጥ አፍራሽ ሀይሎች በየቀኑ የሚፈጥሩት ሴራና ተንኮል እንዲከሽፍ ፣ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀግብር እንዲሳካ፤ እንዲሁም የድሬዳዋ አስተዳደርን ጨምሮ በአገር አቀፍ ደረጃ በተደረገው ፍትሀዊና ሰላማዊ ምርጫ የናንተን ይሁንታ አግኝቶ በተመረጠው ፓርቲ በቅርቡ የሚመሰረተው አዲስ መንግሥት የልማትና የብልፅግና ትልሙ እንዲሳካ ፤ የመላው ሕዝብ የነቃ ተሣትፎ ወሣኝ በመሆኑ፤ ሁላችሁም የበኩላችሁን በጎ አስተዋጽኦ እንድታበረክቱ በዚሁ አጋጣሚ የአክብሮት ጥሪዬን እያቀረብኩ፤ በአሉ የሰላም፣ የፍቅርና የአንድነት በአል እንዲሆንላችሁ ከልብ እመኛለሁ ።
አመሰግናለሁ፡፡
ሐምሌ 12 /2013 ዓ.ም
ምንጭ፦ድሬዳዋ ከንቲባ ፅ/ቤት


