በሀገራችን ኢትዮጲያ ላይ ግልፅ ጦርነት ያወጀውን ከሀዲውን ጁንታ በአደባባይ በማውገዝና ለሀገር መከላከያ ሰራዊታችን ያለንን ክብርና ድጋፍ የምንገልፅበት እንዲሁም 2 ተኛው ዙር የታላቁ የኢትዮጲያ ህዳሴ ግድብ ግንባታ የውሀ ሙሌት መጠናቀቅ ብስራትና ደስታ የምንገልፅበት ብሎም ሰላማዊ ዲሞክራሲያዊና በህዝብ ዘንድ ታአማኒነትን ያተረፈውን 6 ዙር ሀገራዊ ምርጫ በሰላም ከመጠናቀቁ ጋር ተያይዞ ደማቅ ሰላማዊ ሰልፍ በድሬዳዋ አስተዳደር የፊታችን እሁድ በለገሀር አደባባይ ላይ እንደሚካሄድ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ እስቂያስ ታፈሰ ተናግረዋል ።
በዚሁም ታሪካዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይም በድሬዳዋ አስተዳደር በከተማም ሆነ በገጠር የሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ፣ ወጣቶች ፣ ሴቶች ፣ ተማሪዎች ፣ ህፃናት ፣ የመንግስት ሰራተኞች ፣ የፌደራል ተቋም ሰራተኞች ፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶችና ሰራተኞች እንዲሁም ሁሉም የከተማዋ ነዋሪዎች በዚህ ታሪካዊ የድጋፍ ሰልፍ ላይ ተገኝተው ድጋፋቸውን እንዲገልፁም አቶ እስቂያስ ታፈሰ ተናግረዋል ።
ይኸውም የድጋፍ ሰልፍ የፊታችን እሁድ ከጠዋቱ 12 ሰአት እስከ 5 ሰአት እንደሚካሄድና ከዚሁ ጋር ተያይዞ በከተማችን አራቱም አቅጣጫዎች የሚገኙ ዋና ዋና መንገዶች ለጊዜው ለትራፊክ ዝግ እንደሚሆኑና የድጋፍ ሰልፍ በሰላም ይጠንቀቅ ዘንድም አሽከርካሪዎች እንዲሁም ተቋማት አስፈላጊውን ትብብር ሊያደርጉ እንደሚገባና የከተማዋ ነዋሪዎችም በድጋፍ ሰልፍ ላይ ሊገኙ እንደሚገባ ነው አቶ እስቂያስ ታፈሰ ጥሪያቸውን ያቀረቡት ።


