የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በሰላም እሴት ግንባታ ዙሪያ አበክረው መስራት እንደሚገባቸው ተገለፀ::
የምስራቃዊ እድገት ፋና የነዋሪዎች የበጎ አድራጎት ድርጅት ከyouth and cultural development foundation(YCDE) ጋር በመተባበር በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የስነ-ዜጋ ትምህርትን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሄደ፡፡ በድሬደዋ ዩኒቨርስቲ በተዘጋጀው የግንዛቤ ማስጨበጫ የሀይማኖት አባቶችና የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የተገኙ ሲሆን በከፍተኛ ትምህርት ቤቶች የሰላም ትምህርት እንደ አንድ የትምህርት አይነት ቢካተት ወጣቱ በሰላም የመኖርና ልማት ላይ የመሳተፍ…


