ሁሉም ዜጋ ለሃገር ልማት በተሰማራበት ዘርፍ የዜግነት ግዳታውን መወጣት እንደሚገባ የድሬደዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ሰራተኞችና ግብር ከፋዮች ገለፁ ::

    የባለስልጣኑ ሰራተኞችና ግብር ከፋዮች የችግኝ መትከል እና የደም ልገሳ ስነስረአት አካሂደዋል።
    በስነስረአቱ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሃመድ ባለስልጣኑ ለሃገር ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ የሆነውን ግብር ከመሰብሰብ ተልእኮውን ከመወጣት ጎንለጎን ስራተኞቹና ደንበኞቹ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባር እንዲሳተፉ እንደሚሰራ ተናግረዋል።
    አክለውም አሁን ላይ እንደሃገር እየተከናወነ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ የበኩላቸውን ለመወጣት እንደዚሁም የአገርን ሰላም ለማስጠበቅ ግዳጅ ላይ ያለውን የመከላከያ ሰራውት ለማገዝ እና ወገንተኝነታችንን ለማሳየት ደም የመለገዝ ተግባር ማከናወናቸውን ተናግረዋል።
    ግብር መክፈልም ሆነ ሌሎች ለሃገር ልማት አስፈላጊ በሆኑ ተግባታት ላይ መሰማራት እንደ ዜጋ ሁሉም የህብረተሰብ ክፍል ሊያከናውነው የሚገባ ተግባር መሆኑን ገልፀው በቀታይም በማንኛውም ሁኔታ የሚቀርቡ አገራዊ ጥሪዎችን ተቀብለን ፈጣን ምላሽ መስጠት ይገባናል ሲሉ በችግኝ መትከል እና በደም ልገሳ ስነስረአቱ ላይ የተሳተፉ የባለስልጣኑ ሰራተኞችና ግብር ከፋዮች ተናግረዋል።