ሁሉም ዜጋ ለሃገር ልማት በተሰማራበት ዘርፍ የዜግነት ግዳታውን መወጣት እንደሚገባ የድሬደዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ሰራተኞችና ግብር ከፋዮች ገለፁ ::
የባለስልጣኑ ሰራተኞችና ግብር ከፋዮች የችግኝ መትከል እና የደም ልገሳ ስነስረአት አካሂደዋል። በስነስረአቱ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ገቢዎች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱሰላም መሃመድ ባለስልጣኑ ለሃገር ኢኮኖሚ ግንባታ ወሳኝ የሆነውን ግብር ከመሰብሰብ ተልእኮውን ከመወጣት ጎንለጎን ስራተኞቹና ደንበኞቹ በተለያዩ የበጎ ፈቃድ ተግባር እንዲሳተፉ እንደሚሰራ ተናግረዋል። አክለውም አሁን ላይ እንደሃገር እየተከናወነ ያለውን የአረንጓዴ አሻራ ዘመቻ የበኩላቸውን ለመወጣት እንደዚሁም የአገርን…


