በስነስረአቱ ላይ የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ አህመድ መሃመድ ቡህ በኢትዮጵያ የምርጫ ታሪክ የተለየ ስፍራ ያለው መሆኑን ገልፀው ዜጎች የሚወክላቸውን በፍላጎታቸው የመምረጥ ህገ መንግስታዊ መብታቸውን መጠቀም መቻላቸውን ገልፀዋል።
10 ፓርቲና 2 የግል ተወዳዳሪ እንደ ድሬደዋ በምርጫው መሳተፋቸውን፣ ምርጫው ውጤታማ እንዲሆን በርካታ አካላት ያሳዩት ተሳትፎ ዲሞክራስያዊ ስረአትን ለመገንባት በተለይም ከምንም በላይ ሃገርን የማስቀደም ዝንባሌ በዳበረ መልኩ የተንጸባረቀበት መሆኑን አቶ አህመድ መሃመድ ቡህ ተናግረዋል።
በሌላ በኩል የድሬደዋ አስተዳደር ምክትል ከንቲባና የንግድ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ ከድር ጁሐር ድሬደዋን ወደፊት አንድ እርምጃ ለማራመድ የሁሉም ዜጋ ድርሻ መሆኑን ተናግረው በቀጣይ ፓርቲያቸው ብልግና ከሁሉም አካላት ጋር በመስራት የድሬደዋን ከፍታ ለማረጋገጥ ጥረት ያደርጋል ብለዋል።


