በመግለጫቸው አራት ዋና ዋና አጀንዳዎችን አንስተዋል-
#ህዳሴ ግድብ ዋንጫ ወደ ድሬደዋ አስተዳደር እንደሚመጣና ለ5 ወራት እንደሚቆይ በቆይታውም ማህበረሰቡን በማስተባበር እንደዚሁም ከተለያዩ የንግድና የግል ተቋማት 30 ሚሊዮን ብር በላይ ለመሰብሰብ መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡
#ከክረምት በጎ ፍቃድ ጋር ተያይዞ በዘንድሮ አመት ከ55 ሺህ በላይ ወጣቶች እንደሚሳተፉ የደም መለገስ ፤የማጠናከሪያ ትምህርት አገልግሎት፤ የአረጋውያን በቶች ጥገና እና ግንባታ እንደዚሁም ጽዳትና የተለያዩ ተግባራትን እንደሚያከናውኑ አስረድተዋል፡፡
#ከአረንጓዴ አሻራ ጋር ተያይዞ ድሬደዋ አስተዳደር 2 ሚሊዮን ችግኝ ለመትከል መታቀዱን ከአስተዳደሩ ባለፈ ከአጎራባች ክልሎች ጋር በመተባበር የችግኝ መትከል ስነስርአት እንደሚካሄድ ከአገር ውስጥ ባለፈ ለጅቡቲ ሪፐብሊክ 200 ሺህ ችግኞችን በማዘጋጀት ለመትከል መታቀዱንም አብራርተዋል፡፡
#ከጎርፍ አደጋ ስጋት ጋር በተያያዘ በያዝነው አመት በከፍተኛ ዝናብ ሳቢያ እንደዚሁም በጎርፍ ምክንያት በከተማችን በተለያዩ አካባቢዎች ከንብረት መውደም እስከ ህይወት መጥፋት አደጋ መድረሱን አስታወሰው ይህ ክስተት ዳግም እንዳይደገም ጎርፍ ሊያስከትሉ የሚችሉ ሁኔታዎችን ህብረተሰቡ ቀድሞ መከላከል እንደሚገባው ምክትል ከንቲባው ጥሪ አቅርበዋል፡፡


