በድሬዳዋ አስተዳደር ባለፍት ሁለት አመት የደም ልገሳ ስርአቱ የተሻለ መሆኑ ተገለፀ ።

    በ 2013 ዓ.ም 5 ሺህ 489 ዩኒት ደም መሰብሰብ መቻሉም ተገልፆል ።
    ደም ከተለያዩ በጎ ፍቃደኛ ከሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሰብስቦ አደጋ ለደረሰባቸው ፣ የደም ማነስ ላለባቸው ፣ በወሊድ ምክንያት ደም ለሚፈሳቸው ፣ የደም ህክምና ለሚያስፈልጋቸው ህሙማን የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ደም ባንክ አገልግሎት ዘርፈ-ብዙ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
    የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ደም ባንክ አገልግሎት በ 2013 ዓ.ም ከበጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች 6 ሺህ ከረጢት ደም ለማሰባሰብ አቅዶ 5 ሺህ 489 ዩኒት ደም መሰብሰብ ተችሏል ይህም አፈፃፀም ከእቅዱ አንፃር 92 ፐርሰንት መሆኑን የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ደም ባንክ አገልግሎት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፋሲል ዘውዴ ተናግረው ይህም አፈፃፀም ከባለፈው አመት አንፃር ሲታይ በዘንድሮው አመት ከፍተኛ የሆነ ደም መሰብሰብ መቻሉንም አቶ ፋሲል ተናግረዋል ።
    በድሬዳዋ አስተዳደር ባለፍት ሁለት አመታት የደም ልገሳ ስርአቱ የተሻለ ከመሆኑም ባለፈ ከጊዜ ወደ ጊዜ የበጎ ፍቃደኛ ደም ለጋሾች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን አቶ ፋሲል ዘውዴ ተናግረው በ 2014 ዓ.ም 6 ሺህ 600 ከረጢት ደም ለማሰባሰብ እንደታቀደና ይሄም እቅድ ይሳካ ዘንድ ብሎም በደም እጦት ምክንያት ህይወታቸው የሚያልፍ ዜጎችን ለመታደግ ይቻል እድሜያቸው ከ 18 አመት በላይ የሆኑና ደም መለገስ የሚችሉ የህብረተሰብ ክፍሎች ደም ሊለግሱ እንደሚገባም የድሬዳዋ ጤና ቢሮ ደም ባንክ አገልግሎት አስተባባሪ የሆኑት አቶ ፋሲል ዘውዴ ተናግረዋል ።