ኡጉጉማ በሚባለው የጥፋት ቡድን በንፁሃን ዜጎች ላይ የተፈፀመውን ግድያና ማፈናቀል ያወገዙት የድሬደዋ ነዋሪዎች የንፁሀንን ደም ያፈሰሱ ወንጀለኞች ለህግ እንዲቀርቡ ጠይቀዋል።
በሰልፉ ላይ ከንቲባ አህመድ ቡህ ፣ ምክትል ከንቲባ ከድር ጁሀር እና የሱማሌ ክልል ንግድ ኢንዱስትሪ ቢሮ ሀላፊ አቶ በሽርን ጨምሮ የአገር ሽማግሌዎች እና የወጣት ተወካዮች መልእክት አስተላልፈዋል።
የአስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮችና
በሺዎች የሚቆጠሩ የድሬዳዋ ነዋሪዎች በተሳተፉበት ሰልፍ ላይ የህግ የበላይነት ይከበር ፣ የገርበኢሴ ነዋሪዎች ፍትህ ይሻሉ የሚሉና የተፈፀመውን ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት የሚያወግዙ መፈክሮች ከፍ ብለው ታይተዋል።
ሐምሌ 21/2013 ዓ.ም
ምንጭ፡-ድሬዳዋ ከንቲባ ፅ/ቤት


