አዲሱን ዓመት (2014) የምንቀበለው በታላቅ ተስፋና ድል መሆኑን የድሬዳዋ አስተዳደር አስታወቀ::

    አዲሱ ዓመት ( 2014 ) ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብና ለድሬዳዋ ነዋሪ የሰላም ፣ የጤና ፣የድልና የብልጽግና እንዲሆን የድሬዳዋ አስተዳደር ይመኛል ፡፡
    በ2013 ዓ.ም የገጠሙንን ውስብስብ ችግሮች ከመንግስታችን እና ከህዝባችን ጋር አልፈን አዲሱን ዓመት ስንቀበል በታላቅ ተስፋና ድል ነው ሲሉ የድሬዳዋ አስተዳደር የመንገስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ አስታወቁ፡፡
    በ2013 ዓ.ም ጁንታው ሀገር በመካድ የሰሜኑን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ሳይታሰብ የወሰደው እርምጃ ሳንወድ በግድ ሀገር የማዳን ግዳጅ ውስጥ እንድንገባና የጀመርናቸውን የልማትና የሰላም ጎዳና ሳንዘናጋ ከመንግስት፣ ከመከላከያ ሰራዊት እና ከህዝባችን ጋር በመሆን ተዓምር ሊባል የሚስችል አኩሪ ተግባር ፈጽመናል በመሆኑም የ2014 አዲስ ዓመት ተስፋና የድል ብስራት ይዞ ይመጣል ብለዋል ፡፡
    ህብረተሰቡም ከመንግስት ጎን በመቆም ያሳየውን ወገንተኝነት በማጠናከር ዘርፈ ብዙ ድጋፉን አጠናክሮ ልማቱን እንዲያፋጥን ጥሪ አቅርበዋል፡፡ መልካም አዲስ ዓመት !!