ጳጉሜ 3 የመልካምነትና የአብሮነት ቀን

    የድሬደዋ አስተዳደር መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ጳጉሜ 3 የመልካምነትና አብሮነት ቀንን በማስመልከት ከቢሮው የማኔጅመንትና ፈጻሚ ባለሞያዎች ጋር የገቢዎች ጤና ቡድን ላሰባሰባቸው ችግርተኛ ተማሪዎችና ለአካል ጉዳተኞች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡
    የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ እስቅያስ ታፈሰ በመርሀ ግብሩ ላይ እንደተናገሩት ጳጉሜ 3/2013 ዓ.ም የመልካምነትና የአብሮነት ቀንን ምክንያት በማድረግ ለችግርተኛና ለአካል ጉዳተኞች ተማሪዎች 20 ሺ ብር የሚገመት የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉን በመግለጽ ይህ ተግባር በቀጣይም መልካም በማድረግ፤ በመተጋገዝ፤ ቅን በመሆንና ሰዎችን በመርዳትና በማገዝ አንድነታችንን በማጠናከር ሀገራችን የያዘችውን የብልፅግና ጉዞ እውን የምናደርግበትና በመሆኑ ሁሉም የሀገራችን ዜጎች ሃላፊነታችንን መወጣት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡
    ድጋፍ የተደረገላቸው የአካል ጉዳተኞች ባለፈው አመት በቢሮው እንደዚሁ ድጋፍ እንደተደረገላቸው ጠቁመው አሁንም ለቢሮው ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ድጋፍ ስለተደረገላቸው በተደረገላቸው ድጋፍ አመስግነዋል፡፡