ዘንድሮ በድሬደዋ የሚከበረው 16ኛው የኢትዮጵያ የብሄር ብሄረሰቦች ቀን አከባበር በተመለከተ ውይይት እየተካሄደ ነው።

    የፌዴሬሽን ምክርቤት አፈ ጉባኤ አቶ አደም ፋራህ እና የድሬደዋ አስተዳደር ከንቲባ አቶ ከድር ጁሃር እተመራ ያለው ይህ ውይይት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች እየተሳተፉበት ይገኛል።ውይይቱ በዓሉን ባማረና የብሄር ብሄረሰቦች አንድነትን በማዳበር ህብረ ብሄራዊ አንድነትን ለማጠናከር በሚያስችል መልኩ ለማክበር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አተኩሯል።