የፌደራል ማረምያ ቤቶች ድሬዳዋ ቅርንጫፍ ለሆስፒታሉ ድጋፍ አድርግዋል ።
የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከዲር ጁሐር በጉብኝቱ ባስተላለፉት መልዕክት ሀገር ምስረታም ሆነ እዲስ ካቢኔ መመስረት የቻልነው የመከላከያ ሰራዊታችን በከፈለው መስዋዕትነት በመሆኑ ያለን ክብር ከፍ ያለ ነው ። ያለውን ጉድለት ተመልክተን በቅርቡ ድጋፍ እናደርጋለን ብለዋል ።
ለምስራቅ እዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል ድጋፍ ያደረጉት የፌደራል ማረምያ ቤቶች ድሬዳዋ ቅርንጫፍ አዛዥ ኮማንደር ወንድሙ ያዘጋጁትን ድጋፍ ( 150 ብርድ ልብስ ፣ 5 ትልቅ ብረት ድስት ፣ 10 የታካሚ ልብስ እና 1 ስትሬቸር ) ለሆስፒታሉ አዛዥ ኮሎኔል ብርሃኑ ካስረከቡ በኋላ ባደረጉት ንግግር የስራ ክፍፍል ሆኖ ከተማ ብንገኝም ልባችን ከመከላከያ ስራዊት ጋር እንደሆነ ገልጸው በተግባርም ለመሳተፍ 300 አባላት መመዝገባቸውን ይፋ አድርገዋል ።
ድጋፉን የተረከቡትየምስራቅ እዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል አዛዥ ኮሌኔል ብርሃኑ ዘውዱ ጠላቶቻችን መንግስት እንዳንመሰርት ቢረባረቡም አዲስ መንግስት በመሰረትን ማግስት የተደረገ ድጋፍ በመሆኑ ደስታዬን እየገለጽኩ ፌደራል ማረምያ ቤቶች ድጋፍ ሲያደርግልን ይህ ይመጀመርያው አለመሆኑን ገልጸው ምስጋና አቅርበዋል ።
በመጨረሻም ለመከላከያ ስራዊት የተዘጋጀውን ማዕድ ከንቲባ ከድርን ጨምሮ የካቢኔ እባክህ ተቕድሰዋል ።
የድሬዳዋ አስተዳደር እዲሱ ካቢኔ የመጀመርያ የስራ ጉብኝቱን የምስራቅ እዝ ደረጃ ሶስት ሪፈራል ሆስፒታል እደረገ::


