መላው የአስተዳደራችን ነዋሪዎች የአሸባሪውን ጁንታ ሴራ በማጋለጥ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሒም ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ፡፡
አረመኔያዊውና አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ጁንታና ተላላኪዎቹ እኔ ያልመራኋት ኢትዮጵያ መፍረስና መበታተን አለባት ብሎ የቁም ቅዠቱን ለመተግበር የትግራይን ወጣቶች አታሎ በኢትዮጵያ ላይ እያዘመተ ለትውልዱ ሳይራራ እየማገዳቸው ይገኛል፡፡ ይህ ርህራሄ የጎደለውና ሰይጣናዊ ባህሪን የተላበሰው አሸባሪ ቡድን በደረሰባቸው ቦታዎች ሁሉ ንፁሃንን በግፍ እየረሸነ፣ እያረደና እያቃጠለ ክፋቱንና አሸባሪነቱን በአደባባይ እያረጋገጠ እንዳለይ ታወቃል፡፡ በመሆኑም ኢትዮጵያ በታሪኳ ከየትኛውም አቅጣጫ ለመጣ ወራሪ…


