መላው የአስተዳደራችን ነዋሪዎች የአሸባሪውን ጁንታ ሴራ በማጋለጥ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ የድሬዳዋ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኢብራሒም ዩሱፍ ጥሪ አቀረቡ፡፡

    አረመኔያዊውና አሸባሪው የሕወሓት ቡድን ጁንታና ተላላኪዎቹ እኔ ያልመራኋት ኢትዮጵያ መፍረስና መበታተን አለባት ብሎ የቁም ቅዠቱን ለመተግበር የትግራይን ወጣቶች አታሎ በኢትዮጵያ ላይ እያዘመተ ለትውልዱ ሳይራራ እየማገዳቸው ይገኛል፡፡
    ይህ ርህራሄ የጎደለውና ሰይጣናዊ ባህሪን የተላበሰው አሸባሪ ቡድን በደረሰባቸው ቦታዎች ሁሉ ንፁሃንን በግፍ እየረሸነ፣ እያረደና እያቃጠለ ክፋቱንና አሸባሪነቱን በአደባባይ እያረጋገጠ እንዳለይ ታወቃል፡፡
    በመሆኑም ኢትዮጵያ በታሪኳ ከየትኛውም አቅጣጫ ለመጣ ወራሪ ኃይል እጅ ሰጥታ የማታውቅ በጀግኖች ልጆቿ ታፍራና ተከብራ የኖረች ሃገር በመሆኗ ጀግናው የመከላከያ ሠራዊት፤ልዩኃይሉ፤ ሚሊሻውና መላው የሀገራችን ህዝቦች ከዳር እስከዳር ተነስተው ይህን ወራሪና አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ ብርቱ ትግል እያደረጉ ይገኛሉ፡፡
    መላው የአስተዳደራችን ነዋሪዎችም ይህ አሸባሪ ጁንታ የፈፀመብንን ወረራና የተደቀነብንን ሃገር የማፍረስ አደጋ ለመቀልበስ እንደከዚህ ቀደሙ ሁሉ ከሀገር መከላከያ ሠራዊታችን ጎን በመቆም የሞራልና የሎጂስቲክ ድጋፍ በማድረግ እንዲሁም በግንባር በመዝመት፤ በየአካባቢያችን የሚንቀሳቀሱ የአሸባሪ ቡድን ተላላኪዎችን በማጋለጥና አሳልፎ በመስጠት ከምንጊዜውም በላይ የአስተዳደራችንን ሰላምና ፀጥታ በማስጠበቅና በጦርነቱ የተፈናቀሉ ዜጎችን በመደገፍ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ እንድታደርጉ ሲሉ ጥሪያቸውን አስተላፈዋል፡፡