ሙስናና ብልሹ አሰራንን በመከላከል በጋራና በአንድነት የሀገራችንን ብልፅግና ማረጋገጥ እንደሚገባ ተገለፀ ።

    በአለማችን ለ 18 ተኛ በሀገራችን ደግሞ ለ 17 ጊዜ የሚከበረው የፀረ ሙስናና የስነ-ምግባር ቀን እንዲሁም 16 ተኛውን የኢትዮጲያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀንን ምክንያት በማድረግ የድሬዳዋ አስተዳደር ኮንስትራክሽን ቢሮ በቢሮው ላሉ ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰጥቷል ።
    በተለይም ሙስና በአለማችን ፣ በአህጉራችን አፍሪካና በሀገራችን ኢትዮጲያ ላይ በስፋት ከመስተዋሉ ጋር ተያይዞ የሀብት ምዝበራዎቹ በጣም በረቀቀ መልኩ ከመካሄዳቸውም ባለፈ ከሙስናው ጋር ተያይዞ የተለያዩ ግጭቶችም እንዲፈጠሩ የማድረጉ ሚና የጎላ ነው ።
    ከዚሁ ጋር ተያይዞም የእኛነታችን ፣ የአንድነታችን ብሎም የማንነታችን መገለጫ የሆነው የብሄር ብሄረሰቦች ቀን በአል መከበሩ በተለይም የኢትዮጲያን አንድነት ለማስጠበቅ የቢሮው ባለሞያ መወጣት ያለበት ሚና ብሎም ከፀረ ሙስናው ጋር ተያይዞም በቢሮው ያሉ ባለሞያዎች ጥሩ የሆነ ስነ-ምግባርን ተላብሰው ህብረተሰቡን ያገለግሉ ዘንድ በማለም የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ መካሄዱን የድሬዳዋ አስተዳደር የኮንስትራክንና ቤቶች ልማት አስተዳደር ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ የሆኑት አቶ ደራራ ኢብራሂም ተናግረዋል ።
    አቶ ደራራ አክለውም ሁሉም ባለበት የስራ መደብና ሀላፊነት የተጣለበትን ሀላፊነት በአግባቡ ከመወጣት አንስቶ ፣ ለህብረተሰቡ በታማኝነትና በቅንነት የተቀላጠፈ አገልግሎት መስጠት ፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊትን መደገፍ እንዲሁም የብሄር ብሄረሰቦችን አንድነትና አብሮነት ማስጠበቅ እንደሚገባም ነው አቶ ደራራ በእለቱ የተናገሩት ።
    በመድረኩ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የቢሮው ሰራተኞች በበኩላቸው የፀረ ሙስና ቀንን እንዲሁም 16 ተኛውን የኢትዮጲያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን በአልን አስመልክቶ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ መካሄዱ በተለይም ሰራተኛው ሙስናና ብልሹ አሰራንን ለመከላከል በቂ እውቀትና ግንዛቤ እንዲኖረው እንዲሁም ሀገራችን ኢትዮጲያ ውስጥ በርካታ ባህል ፣ ቋንቋ ፣ ሀይማኖት ፣ እሴቶች እንደመኖራቸው መጠን እነዚህን በሚገባ ለማወቅና በቂ የሆነ ልምድ ለመቅሰምና ለመለዋወጥ አይነተኛ አስተዋፆ እንደሚኖረውም ነው ተሳታፊዎቹ የተናገሩት ።